Hellina Nigatu

View My GitHub Profile

layout: page title: “ህሊና ንጋቱ” permalink: /amharic/

Screenshot from 2024-01-25 12-35-43

ህሊና ሀይሉ ንጋቱ | Hellina Hailu Nigatu

📧 hellina underscore nigatu at berkeley dot edu

በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ካሊፎርኒያ በርክሌይ በEECS ዲፓርትመንት የሁለተኛ ዓመት ፒ.ኤች.ዲ ተማሪ ነኝ። የመጀመሪያ ዲግሪዬን በኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና አጠናቅቄያለሁ። በአሁኑ ጊዜ በፕሮፌሰር ሳራ ቻሲንስ እና በፕሮፌሰር ጆን ካኒ ስር ፒ.ኤች.ዲዬን እየሰራሁ እገኛለሁ። የPLAITCannyLab እና BAIR አባል ነኝ።

የእኔ የምርምር ፍላጎት በሰፊው በ AI(ሰው-ሰራሽ አስተውሎት) እና HCI መገናኛ ላይ ያተኮረ ሲሆን AI መሳሪያዎችን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነው። የናቹራል ላንጉጅ ፕሮሰሲንግ መሳሪያዎችን በቂ ዴታ ለሌላቸው ቋንቋዎች ተደራሽ በማደረግ ላይ እየሰራሁ እገኛለሁ። እንዲሁም AI በህብረተሰብ ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገራት እና በአለምአቀፍ ደቡብ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን እንዴት እንደሚጎዳ አጠናለሁ።

ከምርምር ውጪ መጽሃፍትን ማንበብ📚 ፣የኢትዮጵያን ባህላዊ ቡና ማዘጋጀት እና መጠጣት ☕፣ ሹራብ መስራት 🧣፣ ጥበብን ማድነቅ 🎨 እና መጻፍ ✍️ እወዳለሁ።

ዜና

ዋድ ስኮላርሺፕ ፕሮግራም ለ2022 ምሁራን መቀበያ ዝግጅት ላይ ተጋባዥ ተናጋሪ ነበርኩ።

SIGHPC ኮምፒውቲሽናል እና ዳታ ሳይንስ ፌሎውሺፕ ከ2022 አሸናፊዎች አንዷ በመሆኔ ደስ ብሎኛል።

በ STEM ውስጥ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር በቢቢሲ አማርኛ በመቅረቤ ደስ ብሎኛል።

ህትመቶች

አንድሪው ማክራብ፣ ህሊና ንጋቱ ፣ አብሳላት ጌታቸው፣ ቫለሪያ ቤርታኮ “ዳይግራፍ፡ ተለዋዋጭ የግራፍ ጀነሬተር እና የቤንችማርክ ስብስብ።” የ5ኛው ACM SIGMOD የጋራ አለምአቀፍ አውደ ጥናት በግራፍ ዳታ አስተዳደር ተሞክሮዎች እና ሲስተምስ (ግራዴስ) እና የአውታረ መረብ ዳታ ትንታኔ (ኤንዲኤ)። 2022

Chris Chinenye Emezue, ህሊና ንጋቱ , Cynthia Thinwa, Lerato Louis, Idris Abdulmumin, Samuel Gbenga Oyerinde, Benyamin Ayoade Ajibade, Helper Zhou, Emeka Felix Onwuegbuzia, Handel Chiagozie Emezue, Ifeoluwatayo Adeseye Ige, Atnafu Lambejeud Igebo, Chigozi Hassan Muhammad, Olanrewaju Samuel። “የአፍሪካ ‘ስቶፕ ቃላቶች’ ፕሮጀክት፡ ለአፍሪካ ቋንቋዎች የ’ስቶፕ ቃላቶችን’ ማዘጋጀት” 3ኛው የአፍሪካ የተፈጥሮ ቋንቋ ሂደት ላይ አውደ ጥናት። 2022

ንግግሮች

ማስተማር

አገልግሎት

ጉግል ስኮላር ትዊተር